=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ሂወታችነን በደንብ ለመኖር እና ከህመም የፀዳ ሂወትን ለመምራት አወንታዊ የሆኑ እርምጃዎችን ልንወስድ ይገባል። ለረዥም ጊዜ በአለም ዙሪያ የሚገኙ የጤና ኬላዎች ህሙማንን በማከም ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። ነገርግን አብዛሃኛዎቻችን እንደምናውቀው ከህክምና ይልቅ አስቀድሞ መከላከል የተሻለ ነው። ትክክለኛ መረጃን መሠረት በማድረግ በስር ሰደድ በሽታዎች ለምሳሌ የልብ ህመም ፣ የስኴር በሽታ ፣ የደም ግፊት ፣ ካንሰር ወ.ዘ.ተ ከመያዛችን በፊት እርምጃ መውሰድ ይኖርብናል።
ትንሽ ነገር ግን በጣም ጠቃሚና መሠረታዊ የኑሮ ዜዴ ለውጥ በማምጣት ደስተኛና ጤናማ ሂወትን መምራት እንችላለን። ጤናማ መሆን ሂወታችነን በደስታ ፣ በሃሴትና በስኬት እንድንኖር ያግዘናል።
መደበኛ የአካል እንቅስቃሴ በማድረግ ፣ በደንምብ በመመገብ ፣ በቂና ተፈላጊ የሆነ የእንቅልፍ ጊዜ እንዲኖረን በማድረግ ፣ ጭንቀትንና ፍርሃትን በማስወገድ ፣ አካላችነን በመቆጣጠር ጥሩ ስሜት እንዲሰማን ማድረግ እንችላለን። ስለራሳችን መልካም ነገር ተሰማን ማለት በአስተሳሰባችን ፣ በማህበራዊ ኑሯችን ወ.ዘ.ተ የተሻልን እንድንሆን ያግዘናል። ይህ በራስ የመተማመን ስሜትም በሂወታችን ማሳካት ለምን ፈልጋቸው ግቦች እንደ ግብአትነት ያገለግላል።
•:☀:.•♥ንቁ መሆን♥•:☀:•
ሁልጊዜ ቲቪ ፣ ቪድዮ ፣ ፊልም ፣ ድራማ እያዩና ጌሞችን እየተጫወቱ ማሳለፍ ፣ ከቅጥ በላይ መመገብ የጤናማ ሂወት የአኗኗር ዘዴ አይደለም። ከአሏህ ህግጋትና ከረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ንግግር ጋር በማይጋጭ መልኩ ንቁ የምንሆንባቸውን መንገዶች መፈለግ አለብን።
•:☀:•♥ምግባችን♥•:☀:•
ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ስርአት ዩኑረን። ይህም ማለት ብዙ መመገብ ማለት ሳይሆን ለአካላችን ጠቃሚና በቂ ንጥረነገሮችን በዕለት ተዕለት ምግባችን ውስጥ እንዲኖረን ማድረግ ማለት ነው። እነዚህ ንጥረነገሮች በአራት ክፍሎች ይከፈላሉ። እነሱም:-
- ቪታሚን
- ፕሮቲን
- ካርቦሃይድሬት
- ሊፒድ
ጤናማ የአመጋገብ ስርአት እንዲኖረን ከሆነ የተለያዩ ምግቦችን መመገብ ይኖርብናል። ከላይ ከተጠቀሱት ንጥረነገሮችም በእያንዳንዱ ምግባችን ሊኖረንም ይገባል። ይህን ማይረጋችን ለእያንዳንዱ የሂወት ጊዜያችን ሃይልና ብርታትን ለማግኘት ሰበብ ይሆኑልናል። ይህን ማድረግ ከቻልን ስለራሳችን መልካም ነገር ይሰማናል፤ በሂወታችንም ውስጥ ለውጥ ማየት እንችላለን።
•:☀:•♥በደምብ መተኛት♥•:☀:•
እንቅልፍ አሏህ(ሱ.ወ.ተ) ለሰው ልጆች ከሰጠው ትልቅ ኒዕማ አንዱ ነው። ቀን ስንለፋ ፣ ስንደክም ፣ ስንባክን የዋልንበትን ጐናችነን እንድናሳርፍ ይረዳናል። የተረጋጋና ንፁህ እምሮ እንዲኖርም የሚያደርግ ሲሆን ሙሉ አካላችን እንዲያርፍና እራሳችነንም ለተሻ ስራ እንድና ነሳሳ ያደርገናል።
•:☀:•♥የራስን ስሜት በራስ መግለፅ
♥•:☀:•
ምን እንደሚሰማን ለሰዎች መግለፅ ለሰዎች ማካፈል በጣም ጥሩ ነገር ነው። ይህን ማድረጋችን እረፍትን ይሰጠናል። እንዴት እራሳችነን ለሰዎች መግለፅ እንዳለብን የምንቸገር ከሆነ እራስንሳችነን የምንገልፅባቸው ብዙ መንገዶች ስላሉ አንዘን። ምን እንደሚሰማን በፅሐሁፍ ፣ በግጥም ፣ በታሪክ ፣ በስዕል ወ.ዘ.ተ እራሳችነን መግለፅ እንችላለን።
•:☀:•♥ እንርጋታ ♥•:☀:•
ሶላትን ተመስጦ በመስገድ ፣ ቁርአን በመቅራት ፣ ዚክር ፣ ዱአና ስቲግፋር በማድረግና ነሺዳውችን በማዳመጥ ከጏደኞቻችን ጋር ጤናማ በሆኑ ነገሮች በመዝናናት እንዲሁም የአካል እንቅስቃሴ በማድረግ ወ.ዘ.ተ የእርጋታ መንፈስን ማዳበር እንችላለን።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|